የጨረታ ማስታወቂያ

የጨረታ ቁጥር፡ ብትድ/የፋ/ያ/ግ/034/2017

ብሔራዊ ትምባሆ ድርጅት /ኢትዮጵያ/ አ.ማ. የተለያዩ አይነት የሰብል (እርሻ) ኬሚካሎችን በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል፡፡

ስለዚህ በተመሣሣይ ሙያ የተሰማሩና የንግድ ፈቃድ ያላቸው ቀጥሎ የተዘረዘሩትን መሥፈርቶች የሚያሟሉ ድርጅቶች በውድድሩ ላይ እንዲሳተፉ ይጋብዛል፣

  1. ተጫራቾች ለዘመኑ የታደሰ የንግድ ፈቃድ፣ የግብር ከፋይነት የምስክር ወረቀት እና የተጨማሪ እሴት ታክስ የምስክር ወረቀት ኦሪጅናልና ፎቶ ኮፒ ጨረታ ለመግዛት ሲመጡ ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
  2. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን የማይመለስ ብር 200.00 (ሁለት መቶ) በመክፈል ማስታወቂያው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ የፋብሪካ ያልሆኑ ዕቃዎች ግዥ ዋና ክፍል ቢሮ ቁጥር 008 በመቅረብ መግዛት ይችላሉ፡፡
  3. ተጫራቾች የጨረታ ዋስትና ማስከበሪያ /ቢድ ቦንድ/ በሚያቀርቡት ጠቅላላ ዋጋ ላይ ከ 1% የላነሰ በባንክ በተመሰከረ ቼክ /ሲፒኦ/ ወይም የባንክ ዋስትና / Bank Guarantee/ ማስያዝ ይኖርባቸዋል፡፡
  4. ተጫራቾች ኬሚካሎችን ለማቅረብ የጨረታ ሰነዱ በሚያዘው መሠረትየሚጠይቁትን ዋጋና ሌሎች ቴክኒካዊ ዝርዝር ሁኔታዎችን በታሸገ ኢንቬሎፕ እስከ ታህሳስ 26 2010 ከቀኑ 8፡45 ድረስ በብሄራዊ ትምባሆ ድርጅት /ኢትዮጵያ/ አ.ማ. መዝገብ ቤት ማስገባት አለባቸው፡፡
  5. ጨረታው ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ታህሳስ 26 ቀን 2010 ዓ.ም ከቀኑ 9፡00 ሰዓት ላይ በዋናው መ/ቤት የስብሰባ አዳራሽ ይከፈታል፣
  6. አሸናፊው ተጫራች የጠቅላላውን ዋጋ 1ዐ% የመልካም ሥራ አፈፃፀም (Performance Bond) ማስያዝ ይጠበቅበታል፡፡
  7. አሸናፊው ድርጅት ቅድሚያ ክፍያ የሚጠይቅ ከሆነ የቅድሚያ ክፍያውን ሙሉ ዋጋ በባንክ ዋስትና ወይም ሲፒኦ ማስያዝ ይኖርበታል፡፡
  8. ድርጅቱ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በከፊል ወይም ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡

ለተጨማሪ ማብራሪያ በስልክ ቁጥር ዐ11 551 ዐዐ 44 /254/ ወይም 0115-538383 መጠየቅ ይቻላል፡፡

ብሔራዊ የትምባሆ ድርጅት /ኢትዮ./አ.ማ.

About this website

This is the corporate website of National Tobacco Enterprise (Ethiopia).

It does not sell, advertise or offer promotions for our products.

Visitors

Today127
Yesterday192
This week319
This month2958
Total99972
Copyright © 2018 National Tobacco Enterprise (Ethiopia) S.C