አዲስ የተሾሙት የብሔራዊ ትምባሆ ድርጅት/ኢትዮ/አ.ማ ዋና ሥራ አስፈጻሚ ሚ/ር ግራንት መዋት የሚከተለውን አስታውቀዋል

የሥራ አመራር ለውጥ ማስታወቂያ

የተከበራችሁ ባልደረቦች፣

በዛሬው ቀን በባለአክስዮኖች እና በዳይሬክተሮች ቦርድ በተደረገው ስብሰባ ላይ ውዱ ሥራ አስኪያጃችን አቶ ግዛቸው ሓጎስ ቦታውን ለመልቀቅ የደረሱበትን ውሳኔ አሳውቀዋል፡፡ በዚህ ምክንያትም የዳይሬክተሮች ቦርድ እኔን ለወደፊቱ የብሔራዊ ትምባሆ ድርጅት ሥራ አስኪያጅ እንድሆን ሾሞኛል፡፡

አቶ ግዛቸው ብሔራዊ የትምባሆ ድርጅትን ከ23 ዓመታት በላይ በታማኝነትና በትጋት ያገለገሉ ሲሆን ከእነዚህ ዓመታት ውስጥም አሥራ አንዱን ዓመታት በሥራ አስኪያጅነት አሳልፈዋል፡፡ በዚህ ወቅትም ለድርጅቱ የላቀ አፈጻጸምና ዕድገት ከማምጣት ባሻገር ታላቅ የአመራር ብቃት አሳይተዋል፡፡ በእነዚህ ዓመታት ለሥራው ላሳዩት ትጋትም በጥልቀት ልናመሰግናቸው እንወዳለን፡፡ ለአቶ ግዛቸው በብሔራዊ የትምባሆ ድርጅት ውስጥ በሥራ አስኪያጅነት ማገልገል ቢየቆሙም የድርጅቱን አመራር በቀጣይነት በአማካሪነት ለመርዳት ፈቃደኛ በመሆናቸው እጅግ ደስተኛ ነኝ፡፡

የብሔራዊ የትምባሆ ድርጅትን አመራር በተመለከተ ባለፉት 18 ወራት ከአቶ ግዛቸው በጣም ብዙ የተማርኩኝ ሲሆን እንደተተኪም ተቀራራቢ የሆነ አመራር ለማሳየት ተስፋ አደርጋለሁ፡፡

በቀጣዩ አመትም ሥራው በተለመደው መልኩ እንደሚቀጥል በአክብሮት እያረጋገጥኩላችሁ ከእናንተ ጋር አብሮ ለመሥራትም ያለኝን ጉጉት እገልጻለሁ፡፡

ውድ ባልደረቦቼ ምንም ዓይነት ጥያቄ ቢኖራችሁ፣ እኔን አግኝታችሁ ለማነጋገር እንዳታቅማሙ፤ እኔም በቻልኩት መጠን ሁሉ ጥያቄያችሁን ለማስተናገድ እጥራለሁ፡፡

ከአክብሮት ሠላምታ ጋር

ግራንት ሞዋት

About this website

This is the corporate website of National Tobacco Enterprise (Ethiopia).

It does not sell, advertise or offer promotions for our products.

Visitors

Today216
Yesterday190
This week1835
This month5467
Total140775

Visitor Info : Unknown - Unknown
Powered by CoalaWeb
Copyright © 2018 National Tobacco Enterprise (Ethiopia) S.C