በ2016 በጀት ዓመት ዕቅድ አፈፃፀም ላይ ውይይት ተካሄደ

የድርጅቱን የ2016 በጀት ዓመት የምርት እና የሽያጭ ዕቅድ አፈፃፀም ለመገምገም እና በ2017 በጀት ዓመት ዕቅድ ላይ ለመነጋገር እ.ኤ.አ. ጃንዋሪ 18 ቀን 2017 ከቀኑ 8፡00 ሰዓት ጀምሮ የድርጅቱ ሠራተኞች እና የሥራ ኃላፊዎች በተገኙበት ውይይት ተካሄደ፡፡

እንደ ሪፖርት አቅራቢዎቹ ገለፃ በዓመቱ ሊመረት የታቀደው 574,912 ካርቶን የተለያዩ ሲጋራዎችን ሲሆን አፈፃፀሙ 460,373 ካርቶን ሲጋራዎችን ነው፡፡ የዓመቱ የምርት አፈፃፀም በመቶኛ 80.1 እንደሆነ ከሪፖርቱ ለመረዳት ተችሏል፡፡ ለምርት አፈፃፀም ማነስ ምክንያቶቹ በሲጋራ መሥሪያ ማሽኖች ላይ ያጋጠሙ የቴክኒክ ችግሮች፣ ተደጋጋሚ በሆነ የኤሌክትሪክ ኃይል መቆራረጥ የተነሳ በGD05 ላይ በተከሰተው የኤሌክትሪክ ብልሽት ምክንያት ማሽኑ እ.ኤ.አ. ከኦገስት 29 እስከ ሴPቴምበር 14 ቀን 2016 ድረስ ከምርት ሥራ ውጪ መሆኑ፤ በፊልተር መሥሪያ ማሽን ላይ ያጋጠመ የቴክኒክ ችግር የሚሉት ዋና ዋናዎቹ እንደሆኑ ከሪፖርት አቅራቢዎቹ ለመረዳት ተችሏል፡፡

ችግሮቹን ለመቅረፍ የተለያዩ የመፍትሔ እርምጃዎች የተወሰዱ ሲሆን፣ እነዚህም፡-

  • መለዋወጫዎች በአፋጣኝ ከውጭ አገር እንዲገቡ መደረጉ፣
  • አዲስ የፊልተር ዘንግ ማሽን ግዥ መከናወኑ እና ተተክሎ ወደ ሥር መግባቱ፣
  • ከጃፓን ቶባኮ ኢንተርናሽናል የቴክኒክ ባለሙዎች እንዲመጡ እና የቴክኒክ ድጋፍ እንዲሰጡ መደረጉ ናቸው፡፡

የትምባሆ ቅጠል ምርትን በተመለከተ ድርጅቱ በበጀት ዓመቱ በአራቱም የትምባሆ እርሻዎቹ 2,655,550 ኪ.ግ. ደረቅ ትምባሆ ለማምረት አቅዶ አፈፃፀሙ 2488500 ኪ.ግ. ሲሆን ይህም በመቶኛ 93.7 መሆኑን በሪፖርቱ ወቅት ተገልጿል፡፡

በ2016 በጀት ዓመት የተመረተው ደረቅ የትምባሆ ቅጠል ምርት ከ2015 በጀት ዓመት ክንውን ጋር ሲነፃፀር በ178,200 ኪ.ግ. ወይም በ7.7% ብልጫ ያለው መሆኑን ከቀረበው ሪፖርት ለማወቅ ተችሏል፡፡

በበጀት ዓመቱ 597200 ካርቶን የአገር ውስጥ እና የውጭ አገር የሲጋራ ምርቶችን ለመሸጥ ታቅዶ አፈፃፀሙ 467,631 ካርቶን ሲጋራዎችን ወይንም የዕቅዱ 78.3% ሆኗል፡፡ በአጠቃላይ በበጀት ዓመቱ ከልዩ ልዩ ሲጋራዎች ብር 2,248,768፣733 ለመሰብሰብ የታቀደ ሲሆን ብር 1,856፣676፣910 ተሰብስቧል፡፡ ይህም የዕቅዱ 82.6% ነው፡፡

የድርጅቱ ሠራተኞች በውይይቱ ወቅት የተለያዩ ጥያቄዎችን ያነሱ ሲሆን ለጥያቄዎቹ አወያዮቹ እና በስብሰባው የተገኙ የማኔጅመንት አባላት ምላሽ ሰጥተዋል፡፡

ከ2016 የዕቅድ አፈፃፀም ውይይት በመቀጠል በ2017 በጀት ዓመት የምርት እና የሽያጭ እቅድ ላይ ውይይት የተደረገ ሲሆን በወቅቱ የተለያዩ አስተያየቶች ተሰጥተዋል፡፡

በመጨረሻም ከ2016 የዕቅድ አፈፃፀም ትምህርት በመውሰድ የ2017 በጀት ዓመት አፈፃፀም የተሻለ እንዲሆን ሠራተኛውም ሆነ ማኔጅመንቱ መረባረብ እንዳለበት አወያዮቹ ማሳሰቢያ ከሰጡ በኋላ ስብሰባው ተጠናቋል፡፡

About this website

This is the corporate website of National Tobacco Enterprise (Ethiopia).

It does not sell, advertise or offer promotions for our products.

Visitors

Today216
Yesterday190
This week1835
This month5467
Total140775

Visitor Info : Unknown - Unknown
Powered by CoalaWeb
Copyright © 2018 National Tobacco Enterprise (Ethiopia) S.C